$ 0 0 በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን 2 ወረዳዎች ሰሞኑን ተቀስቅሶ የነበረው ግጭት በአካባቢው ህብረተሰብ ጠንካራ ተሳትፎ በቁጥጥር ስር መዋሉን መንግስት አስታወቀ፡፡ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና ጉዳት መንግስት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ገልጿል፡፡ ግጭቱ የሀገሪቱን ሰላም በማይሹ ኃይሎች የተቀሰቀሰ መሆኑን የገለፀው መንግስት እጃቸው እንዳለበት የተጠረጠሩ 43 ሰዎች እስካሁን በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ገልጿል፡፡ ዳዊት ጣሰው፡፡