Quantcast
Channel: ETHIO CLIP - RSS Feed
Viewing all articles
Browse latest Browse all 38142

አጋዚ 3 ሰዎችን በቢሾፍቱ መግደሉን ተከትሎ እናት አምርረው ሲያለቅሱ የሚያሳይ ቪዲዮ

$
0
0

Zehabesha.com
የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮች በቢሾፍቱ 3 ወጣቶችን ገደሉ | እናት በአደባባይ እያለቀሱ ነው

(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች 4ኛ ቀኑን የያዘውን ሰላማዊውን ከቤት ያለመውጣትና ያለመገበያየት አድማ ተከትሎ ወትሮም ሰውን ለመግደል የማይራሩት የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮች ዛሬ በቢሾፍቱ (ደብረዘይት) ከተማ 3 ወጣቶችን በጥይት ቆልተው መግደላቸው ታወቀ::

በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች ሕዝብ ሰላማዊ ትግል እያደረገ ቢሆንም የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮች እና ስናይፐሮች በየከተማው ፈሰዋል:: በቢሾፍቱ ዛሬ ከተገደሉት 3 ወጣቶች መካከል ሁለቱ ታውቀዋል:: በአጋዚ ጥይት ሰለባ የሆኑቱም ተረፈ ሽብሩ እና በቀለ ዲባባ ሲሆኑ የአንደኛው ማንነት እየተጣራ ነው:: በተጨማሪም በርካታ የቆሰሉ ሰዎች እንዳሉ ይነገር እንጂ ዘ-ሐበሻ ለማረጋገጥ አልቻለችም::

ከዛሬው የቢሾፍቱ ግድያ በኋላ በተለይ የበቀለ እናት በአደባባይ ሲያለቅሱ የሚያሳይ ቪዲዮ ተለቋል ይመልከቱት:: የእናቶች ለቅሶ የሚያበቃው መቼ ነው??

Viewing all articles
Browse latest Browse all 38142